Skip to content

Instantly share code, notes, and snippets.

@JaniMohammed
Created February 9, 2018 12:54
Show Gist options
  • Star 0 You must be signed in to star a gist
  • Fork 0 You must be signed in to fork a gist
  • Save JaniMohammed/b7e04a81198447403524cec1e4bd5763 to your computer and use it in GitHub Desktop.
Save JaniMohammed/b7e04a81198447403524cec1e4bd5763 to your computer and use it in GitHub Desktop.
ዓለማፈር
የቀመስኩት ከንፈር
ቀመሰ አሉኝ አፈር
እውነት ያንተም ነገር ላፈሩ ደረሰው?
እኔ የቀመስኩትን አፈሩም ቀመሰው?
በላው አሉኝ አፈር: አፈር አፈር ይብላ
ያን የሀሴት ባህር ያንን እሸት ገላ
ያን ጥዑም ቃና ከማር ከወለላ
አይጠገቤውን ቢበላ ቢበላ
በላው አሉኝ አፈር
አቤት አለም አፈር!
ያፈሩ አለማፈር
ውበት ሲሰለቅጥ ደርሶ አለመግደርደር
የነሱ አለማፈር
በላው ሲሉኝ አፈር
የሱም አለማፈር
ያነጠው በዐፈር
ያነጠበት አፈር
ኪራዩ ሲያበቃ
ውባ ውቡን ህንፃ
አፍርሶ እንደ 'ቃቃ
ያበጀውን አፈር
ወዳፈር መለሰ
ዳቦ ተቆረሰ...ጨዋታ ፈረሰ::
Sign up for free to join this conversation on GitHub. Already have an account? Sign in to comment