Skip to content

Instantly share code, notes, and snippets.

@JaniMohammed
Created February 9, 2018 13:20
Show Gist options
  • Star 0 You must be signed in to star a gist
  • Fork 0 You must be signed in to fork a gist
  • Save JaniMohammed/d382e218239fbd84175000bbd170fa40 to your computer and use it in GitHub Desktop.
Save JaniMohammed/d382e218239fbd84175000bbd170fa40 to your computer and use it in GitHub Desktop.
Poem
እኮ ለምን *
ለምን ቀሰቀስከኝ ምነው ብተኛበት፣
ባትጠራኝ መልሰህ ርቄ ከሄድኩት፣
ፍቅርን ሸሽቼ ከተሸሸኩበት፣
በራሴ ገዳም ውስጥ መናኝ ከሆንኩበት፣
ለምን ቀሰቀስከኝ ምነው ባገኝ እረፍት፣
አልፏል ማንነቴ ተቀብሯል ሙት ሆኖ፣
ያ የተንገላታው ባንተ ፍቅር በግኖ፣
በናፍቆት ወላፈን በጭሱ ታፍኖ፣
በርዶ ላይበርድለት ላይሰክን ገፍሎ፣
እኔነቴ ሄዷል ከኔ ተነጥሎ፣
አትጥራው መልሰህ ከሸሸበት ይኑር፣
ሙት ነው አትፈልገው ባይገባም ከአፈር፣
ለምን ቀሰቀስከኝ፣
ህይወት ልትዘራብኝ ወይስ ልትገለኝ፣
ከወጋኸኝ ወዲያ ይማርሽ ልትለኝ፣
ንገረኝ በል ልስማህ ዛሬ ምኔ ታየህ፣
ኮስማናው ገላዬ ቆይ ምኑ አማረህ፣
የገረጣው ፊቴ ይሄ አመድ ለባሽ፣
የደከመው እግሬ ካንተ ርቆ ሲሸሽ፣
የዛለው ጉልበት መክኖ ስለፍቅርህ:
እንዲ ተጎድቼ ለምን ትመጣለህ፣
ለምን ቀሰቀስከኝ ቆይ ዛሬ ምን ታየህ፣
አየህ አይደለ ካፈር ተማስዬ፣
በጉጬ ሲራመድ አያባሬ እንባዬ፣
በቁዘማ ሲያልፍ በሀዘን ጊዜዬ፣
ወድጄው ነበረ ይሄንን ስቃየን፣
ከሰው ተለይቼ የብቻ ውሎዬን፣
የብቻ ኑሮዬን፣
የብቻ ህይወቴን፣
የብቻ ማንባቴን፣
የብቻ ለቅሶዬን፣
ወድጄው ነበረ፣
ለምን ቀሰቀስከኝ ለምን አለው አልከኝ፣
አረ ልጠይቅህ ቆይ ለምን ጠራኸኝ፣
ምነው ቄስ ቢጠራኝ ብገባ ካፈሩ፣
ዳግም ባልሰማቸው ወፎች ሲዘምሩ፣
አቤት ባልላቸው ወዳጆች ሲጣሩ፣
መቼም ላይከፈት በተዘጋ በሩ፣
ግን እስካለሁ እዚ ትተህ አተወኝም፣
በቁምህ ባላይህ በህልሜ አትቀርም፣
አረ ልተኛበት ጎኔን ላሳርፈው፣
ባክህ አትቀስቅሰኝ እለምንሀለው፣
ሽፋሽፍቴም ፈራ ሊጋጠም ሊዘጋ፣
በህልመ ሰመመን ካንተጋ ሳወጋ፣
ስቃዬን ሲያበዛው ምተኛበት አልጋ፣
መተኛት ፈራሁኝ እንቅልፍን ሸሸሁኝ፣
ዳግም ላላገኝህ ለምን ቀሰቀስከኝ፣
Sign up for free to join this conversation on GitHub. Already have an account? Sign in to comment